ፕላን ማለት መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ ልማት ፕ...

image description
- ውስጥ ዜና    0

ፕላን ማለት መዋቅራዊ ፕላንና የአካባቢ ልማት ፕላን እንዲሁም በህግ የተደነገጉ ሌሎች ፕላኖችን ያጠቃልላል

ገፀ-ምድራዊ ፕላን ማለት በመሬት ላይ፣ በመሬት ዉስጥ እና ከመሬት በላይ ጊዜን፣ ጉልበትን ፣ዕዉቀትን፣ ክህሎትን ፣ ገንዘብንና ቁሳቁሳዊ ሀብቶችን በቁጠባ፣ በተሳለጠ እና ዉጤታማ በሆነ መልኩ በመጠቀም ልማትን ለማካሄድ እንዲቻል / በሁለት እና/ወይም በሶስት ጎንዮሽ መለኪያ በስዕልና በጽሁፍ የሚዘጋጅ መሬት ልማት ተኮር ፕላን ሲሆን መዋቅራዊ ፕላንን፣ የአካባቢ ልማት ፕላንን፣ የመሰረተ ልማት ቅንጅት ፕላንን የዉስጥ ለዉስጥ መንገድ ፕላን/ዲዛይንን እና የመሳሰሉትን ያካትታል፤

መዋቅራዊ ፕላን ማለት በማህበራዊ፣ በምጣኔ ሀብታዊ እና በአካባቢያዊ ዘርፎች የተመጣጠነ የከተማ ልማት ለማስገኘት በሚያስችል መልኩ የከተማን ፊዚካላዊ ዕድገት እና ልማት በተመለከተ መሟላት የሚገባቸዉ ጉዳዮችን የሚዘረዝር እና ህጋዊ ተፈጻሚነት ያለዉ አብይ የከተማ ፕላን ነዉ፤

የአካባቢ ልማት ፕላን ማለት በስልታዊ ባህሪያቸዉ ምክንያት በተመረጡ አካባቢዎች ላይ በማተኮር የከተማዉን አንድ አካባቢ ለማሻሻል ፣ለማደስና ለማስፋፋት በመካከለኛ የዕቅድ ዘመን በጊዜ እየተከፋፈሉና እየተቀናጁ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን የሚያሳይና መዋቅራዊ ፕላኑን በተመረጡ አካባቢዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የልማት ግቦችን ፣አበይት ተግባራትን ፣የአፈጻጸም ስልቶችን ፣የፈጻሚ አካላትን ሚና እና ተፈላጊ ተቋሞችን ፣የአካባቢ ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴን ፣የከተማ ዲዛይን መርሆዎችን ፣ተጨባጭ መስፈርቶችን ፣ የአካባቢ ማዕቀፍን ፣በጀትንና ጊዜን በዝርዝር የሚያሳይ ህጋዊ ተፈጻሚነት ያለዉና መዋቅራዊ ፕላኑ ተግባራዊ የሚደረግበት ፕላን ነዉ፤
የሰፈር ንድፍ ፕላን ማለት በአንድ አካባቢ ወይም ሰፈር የመኖሪያ ስብስብ ዉስጥ መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማካተት ከአካባቢ ልማት ፕላን ቀጥሎ የሚመጣ በፕሮጀክት ደረጃ የሚዘጋጅ ፕላን ነዉ፤

የከተማ ንድፍ ፕላን ማለት መዋቅራዊ ፕላን ወይም የአካባቢ ልማት ፕላን ቦታን ወይም አካባቢን መሰረት በማድረግ መሬት አጠቃቀምን አካቶ ፕላንን ወደ መሬት ለማዉረድ የሚያስችል ዝርዝር የህንጻ ግንባታ የሚያርፍበትን ቦታ ፣በአካባቢዉ የሚገነቡ ግንባታዎች የሚኖራቸዉን መስተጋብር እና የፊት ለፊት ገጽታ ወስኖ የሚያስቀምጥ ፣መሰረተ ልማት መስፈርቶችን የማከፋፈያ ቦታዎችን የሚያመለክትና የሚያስፈልገዉን የአገልግሎት መጠን ጨምሮ መግለጽ የሚችል ሲሆን የቦታ ስፋቱ በአንድ የአካባቢ ልማት ፕላን የተዘጋጀ የቦታ ስፋትን የሚያጠቃልል ወይም እንደአስፈላጊነቱ ባነሰ የቦታ መጠን ሊዘጋጅ የሚችል ፕላን ነዉ፤

ማጠቃለያ ሰነድ ማለት የመዋቅራዊ ፕላኑን የጥናት ዉጤቶችና ልዩ ልዩ ክፍሎችን እንዲሁም የፕላኑን የመሬት አጠቃቀም አመዳደብ መፍቻ የያዘ የፕላን ማጠቃለያ መድብል ነዉ፤

***
ትንታኔዉን በስፓሻል ፕላን ዝግጅት ዘርፍ የጂ አይ ኤስ ባለሙያ አቶ ኢሳያስ ተሾመ ሰጥተዋል፡፡
 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.