ከተማዋ እያስመዘገበች ላለው ሞዴል የዘመናዊነትና የስልጣኔ ማማ ተምሳሌትነት የፕላን ተገዢነትና መሪነት የጎላ ድርሻ አለው፡- አቶ አደም ኑሪ
ከተማዋ እያስመዘገበች ላለው ሞዴል የዘመናዊነትና የስልጣኔ ማማ ተምሳሌትነት የፕላን ተገዢነትና መሪነት የጎላ ድርሻ አለው፡- አቶ አደም ኑሪ
ይህ የተገለፀው የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ የከተማ ፕላን ዝግጅት ስራዎችን፣ የገፀ-ምድራዊ ፕላን አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ክንዉኖችን፣የፕላን ትግበራ ፋይዳዎችን፣ በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ የሃሳብ ዕቅድ አፈፃፀምን፣ የዐንድ ዕቅድ ዐንድ ሪፖርት፤ዐንድ ምዘና ዐንድ ዕውቅናን ዘመናዊ ፕላን ከምትመራ ከተማ ጋር በማገናዘብ ከቢሮዉ ተዋረዳዊ አደረጃጀት ኃላፊዎች ጋር ባካሄዱት የስራ ግምገማ ወቅት ነው፡፡
በስራ ግምገማው የቢሮዉ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ የተካሄደውም ንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካቢኔ አዳራሽ ነው፡፡
የዘመናዊነትና የስልጣኔ ተምሳሌትነት ግስጋሴ ሪፖርትን ያቀረቡት በቢሮዉ የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ አንዋር አክመል ከተማዋን ጥራት ያለውና ተተግባሪ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ፕላን በማዘጋጀትና ትግበራዉን ክትትል ቁጥጥር በማድረግ የተጀመረዉን የዕድገትና ብልፅግና ጉዞ እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡
እንደ አቶ አንዋር ገለፃ፤ አገልግሎቶችን በስታንደርድ በመስጠት ተገልጋዮችን ካላስፈላጊ ምልልስና ወጪ መታደግ ተችላል፡፡
በቢሮዉ በርካታ ፕላኖች ተዘጋጅተዉ በመተግበራቸው 10,917 ባለይዞታዎች ያቀረቧቸዉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሔ ተሰጥቷል ያሉት በቢሮዉ የመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅትና ምላሽ ሰጪ ዳይሬክተር አቶ ዑመር ደሴ ናቸው፡፡
በመጨረሻም የቢሮ ኃላፊዉ አቶ አደም ኑሪ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራት ከአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር፣ ከሪፎርም ስራዎች አንፃር፣ ብልሹ አሰራርን መከላከል፣ ቴክኖሎጂ ማዘመን ላይ የጀመርናቸዉ ስራዎች የተደራሽነታቸዉ ደረጃ በትጋትና በጥራት በመተግበር በዘመናዊ ፕላን የምትመራ የበለፀገችና የለማች ከተማ የመገንባት ራዕያችንን እናሳካለን ብለዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.