ቢሮዉ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት 2,329...

image description
- ውስጥ ዜና    0

ቢሮዉ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት 2,329 የመዳረሻ መንገድ ይከፈትልኝ፣ መንገድ ይነሳልኝና ተያያዥ የውስጥ ለውስጥ ጥያቄዎችን ምለሽ መስጠቱ ተገለፀ፡፡

ቢሮዉ ባለፉት አምስት የለውጥ ዓመታት 2,329 የመዳረሻ መንገድ ይከፈትልኝ፣ መንገድ ይነሳልኝና ተያያዥ የውስጥ ለውስጥ ጥያቄዎችን ምለሽ መስጠቱ ተገለፀ፡፡

(ፕላንና ልማት ቢሮ፤ ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም)

በቢሮዉ የመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅትና ምላሽ ሰጪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዑመር ደሴ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተለያዩ አካላት የቀረቡ 2,329 የመዳረሻ መንገድ ይከፈትልኝ፣ መንገድ ይነሳልኝና ተያያዥ የውስጥ ለውስጥ ጥያቄዎችን በጥናት በመመለስ የከተማዋን ነዋሪዎች ጥያቄዎችና ቅሬታዎች መመለስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

በቢሮዉ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከከተማ ፕላን መረጃና ስታትስቲክስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተሻለ አለሙ ጋር ባደረገው ቆይታ ከለውጡ ወዲህ በማዕከል እና በክፍለ ከተሞች የፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተጠኑና የሚጠኑ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ዘመናዊ የመረጃ አደረጃጀት ሥርዓት በመፍጠር ወቅታዊ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ተዘጋጅቷል፤ ለመሶብ አንድ አገልግሎትም ጥቅም ላይ ውሏል ብለዋል፡፡


በተያያዘም በቢሮዉ የከተማ መሰረተ ልማት ቅንጅት ፕላን ዝግጅትና አፀዳቂ ቡድን መሪ አቶ በረከት ፍቃዱ በበኩላቸው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጥናት ሲካሄድ ከመንገድ ጥናት ውጭ ያሉ ላየሮችን በማሰባሰብ፣ የ2ኛው ዙር የመዋቅራዊ ፕላን ማሻሻያ የመሬት አጠቃቀም ላይ ያለውን የመንገድ መረብ ከመዋቅራዊ ፕላን የመንገድ መረብ ጋር ተናባቢ መሆኑን በማረጋገጥ፣ በመንገድ ተዋረድ ጥናት መሰረት መንገዶችን በድጋሜ በስታንደርዳቸው(Line Type, Color, Line Weight) መሰረት በማደራጀት ነው ብለዋል፡፡

ቢሮዉ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጥናት በማከናወን ነዋሪዎች ትክክለኛና ወጥ መረጃ እንዲያገኙ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር እንዳይፈጠር እየሰራ እንደሆነም አቶ በረከት አክለዋል፡፡ አገልግሎትም በውስጥ ለውስጥ መመሪያ እና የአሰራር መሰረት እንደሚሰጥም ተነግሯል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.