እየተለወጠች በምትገኘው አዲስ አበባ የአገልግሎት...

image description
- ውስጥ ዜና    0

እየተለወጠች በምትገኘው አዲስ አበባ የአገልግሎት ዘርፉን ማሻሻል መቻላችን በሌሎች ስራዎች ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች እንዲሳኩ የማድረግ አቅም አለው፡- ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ

እየተለወጠች በምትገኘው አዲስ አበባ የአገልግሎት ዘርፉን ማሻሻል መቻላችን በሌሎች ስራዎች ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች እንዲሳኩ  የማድረግ አቅም አለው፡- ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ

ሰባተኛው የአዲስ መሶብ ዲጅታል
ማዕከሉን መርቀው ስራ ያስጀመሩት ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ የአገልግሎት ዘርፉን ማዘመንና ፈጣን ማድረግ የህዝባችንን ጥያቄ ከምንመልስባቸው አጀንዳዎች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ም/ከንቲባው አቶ ጃንጥራር ከህዝብ ጋር ስንመክር ስንወያይ በአዲስ አበባ ከተማ በፕሮጀክትና በሃብት አስተዳደር ውጤት እንዳመጣችሁ ሁሉ በአገልግሎት ዘርፉም ለውጥ አምጡልን የሚል ጥያቄን የአንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎቱ ምላሽ እያስገኘ ነው ብለዋል።

እየተለወጠች በምትገኘው አዲስ አበባ የአገልግሎት ዘርፉን ማሻሻል መቻላችን በሌሎች ስራዎች ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች እንዲሳኩ የማድረግ አቅም አለው።

በዚህ ረገድም የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጅታል አገልግሎት ተገልጋዩ ጊዜውን ጉልበቱንና ወጭን በመቆጠብ  በአጭር ጊዜ አገልግሎት እንዲያገኝ እያስቻለ ነው።

ዛሬ የተመረቀው የአዲስ መሶብ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ማዕከል ሰፊ የስራ ቦታ ያለው በመሆኑ ተጨማሪ ስራዎችን ለማስጀመር አመቺ  መሆኑን ታሳቢ ያደረገ ነው።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.