የፕላን ህግጋቶችን ጠብቀዉ የተተገበሩ ፕላኖች የ...

image description
- ውስጥ ዜና    0

የፕላን ህግጋቶችን ጠብቀዉ የተተገበሩ ፕላኖች የከተማዋን ዓለምአቀፍ ደረጃና ሽፋን እያሳደጉ ነው፡- አቶ አደም ኑሪ

የፕላን ህግጋቶችን ጠብቀዉ የተተገበሩ ፕላኖች የከተማዋን ዓለምአቀፍ ደረጃና ሽፋን እያሳደጉ ነው፡- አቶ አደም ኑሪ  

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ምቹ የመኖሪያ፣ የመስሪያ፣ የቱሪስት መዳረሻ የፈጠሩና የከተማዋን ዓለምአቀፍ የዲፕሎማሲ ማዕከልነት ደረጃና ሽፋን ያሳደጉ ጥራት ያላቸው የገፀምድራዊ፣ የማህበራዊና የምጣኔ ሀብታዊ ፕላኖች ተዘጋጅተው ባለፉት የለውጥ ዓመታት ተተግብረዋል፤ በዚህም የህብረተሰቡንም ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡ 

አቶ አደም አያይዘውም፥ ባለፉት የለውጥ ዓመታት፦ ቢሮዉ የአካባቢ ልማት ፕላኖችን፣ የኮሪደር ልማት ፕላኖችን፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕላን፣ የሠፈር ፕላኖችን እንዲሁም የከተማ ዲዛይን በማሻሻል በከተማዋ የላቀ እድገትና ብልፅግና እንዲመዘገብ እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ይህ ውጤትም በፌደራል እና  በከተማ አስተዳደሩ 24/7 የስራ ባህል፣ በቁርጠኛ አመራር፣ የሴክተር ተቋማት ተናቦ መስራት፣ የፕላን ተግባሪ ተቋማት የፕላን ህግጋትን አክብረዉ ከቢሮዉ ጋር በቅንጅት መስራት እንደ መልካም ምክንያት የሚጠቀሱ መሆናቸዉን አቶ አደም አክለዋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.