ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

image description
- ውስጥ ዜና    0

ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!

የዛሬው በጣም ልዩ ነው።

ህዝብ ቤቱ የቀረ እስከማይመስል ድረስ ገና ጎህ ሳይቀድ ወደ መስቀል አደባባይ በመትመም በሚገርም ስሜትና በደስታ እየጨፈረ ድጋፉን ገልፆልናል።

ይህ የድጋፍ ሰልፍና የምረጡኝ ቅስቀሳ የማጠቃለያ መርሀግብር ነው። ልትደግፉን፣ ልታበረታቱን እንቅልፋችሁን ትታችሁ በለሊት ወደ መስቀል አደባባይ የተመማችሁ ውድ የከተማችን ነዋሪዎችን በራሴና በፓርቲዬ ብልፅግና ስም እጅግ አድርጌ አመሰግናሁ! እናከብራችኋለን !!

ለዓለም አንድ ታላቅ መልዕክት አስተላልፋችኋል፤ ኢትዮጵያውያን በምርጫ ብቻ እንደሚያምኑና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መገንባት እንደሚችሉ፤ መንግስትን በምርጫ፣ በህዝብ ይሁንታ ማፅናት የሚችሉ ብርቱ ህዝቦች መሆናችንን ለዓለም ያረጋገጥንበት በመሆኑ፣ አዎን ! ክብር ይገባችኋል።

ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ብቻ ሳይሆን፣ ይልቁንም የተረጋጋ የፖለቲካ ሥርዓት የማፅናት፣ ዘላቂ ሰላምን የማረጋገጥ፣ የተጀመሩትን የልማት ስራዎች የማስቀጠል ፅኑ መንገድ እና ሂደት ነው ።

ስልጣን በምርጫ እንጂ በጉልበት ወይም እንደ ቅርጫ የሚከፋፈል አይደለም፤ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የምናፀናበትና ህዝባችን የሉዓላዊ ስልጣን ባለቤት መሆኑን የምናስመሰክርበት ነው።

የፖለቲካ ስልጣን ከህዝብ ይሁንታ ውጭ ሊሳካ አይገባውም፤ ዳግም ምረጡን ብለን በብዙ የምንጎተጉታችሁ ከእናንተ ድምፅ ውጭ ወደ ሥልጣን የምንመጣበት ሌላ መንገድ እንደሌላ ሥለምናምን ነው።

በመሆኑም፣ 7ኛውን ምርጫ ዴሜክራሲያዊ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ ማድረግ አንዱና ዋናው ግባችን ነው ።

እስከ አሁን ባለው ጉዟችን ብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ስልጣን የሚመነጨው ከህዝብ ይሁንታ መሆኑን በማመን ሃሳባቸሁን በሰላማዊ መንገድ ያራመዳችሁ እና የተከራከራችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም ክርክሩን እና ውድድሩን ለህዝብ ያደረሳችሁ ሚዲያዎች ሁሉ በአጠቃላይ ስልጣን ከህዝብ ድምፅ ብቻ የሚመነጭ እንዲሆን ፅኑ ዴሞክራስያዊ ስርዓትን ለመግገንባት የሰራችሁ ሁሉ ታላቅ ክብር ይገባችኋል።

እስከአሁን ሃሳባችንን ገልፀን ተከራክረናል፣ በሃሳብ ሞግተናል፣ ህዝባችን አዳምጦናል፤ ከዚህ በኋላ ህዝባችን ጥሩ ዳኛ እንደሆነ አምነን በፅናት እንዲወስን እንጠብቀው።

እስከ ዛሬ በሃሳባችሁ፣ በጉልበታችሁ፣ በገንዘባችሁ፣ በእውቀታችሁ በጉዟችን ሁሉ ደግፋችሁን አብራችሁን የነበራችሁ የከተማችን ነዋሪዎችን ከልብ እናመሰግናለን!

መንገዳችን መደመር ነው፤ መዳረሻችን ብልፅግና ነው!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.