የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
የ2018 የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሰኔ 8 እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚሰጠው የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በ199 የፈተና ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።
ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ በየደረጃው የኮማንድ ፖስት አደረጃጀት የማዋቀር እና ልምድ ያላቸውን የፈተና አስፈጻሚዎች በመመልመል በየፈተና ጣቢያው ከመመደብ ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ 85 ሺህ 17 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን ለመውሰድ ተመዝግበው ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡
በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የፈተናውን ሂደት የሚከታተሉ አመራሮችን ጨምሮ የጸጥታ አካላት እና የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸውን አመላክተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የተማሪዎች የምገባ አገልግሎት ተግባራዊ መሆኑ እንዲሁም ዩኒፎርምን ጨምሮ የተለያዩ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ በየዓመቱ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ዶክተር ዘላለም አስታውሰዋል፡፡
ዘንድሮ ከተደረገው የቅድመ ዝግጅት ሥራ አንጻር በ6ኛ ክፍል የተሻለ ውጤት እንደሚጠበቅም መጥቀሳቸውን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.