የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ለተገልጋዮች የቀረበ አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡- አቶ አደም ኑሪ
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ለተገልጋዮች የቀረበ አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡- አቶ አደም ኑሪ
(ፕላንና ልማት ቢሮ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ ለተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ለክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎችና አስተበባሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በቢሮዉ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደተናገሩት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የመንግስት ተቋማት አሰራርን በማዘመን ስታንደርድን መሰረት ያደረገ፣ ለተገልጋዩ ህብረተሠብ ቀልጣፋና ዉጤታማ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሃብት ልማት ቢሮ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ የሪፎርሙ ዓላማ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት እንዲሁም ብዝሃነትንና አካታችነትን ያረጋገጠ ለልማት ግቦች ስኬት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ነጻ ፣ገለልተኛና ብቁ ባለሙያ መገንባት መሆኑን ስልጠናውን በሰጡበት ወቅት ገልጸዋል። ኢንዱስትሪን መሰረት ያደረገ የተቋም ግንባታ ለመስራትም ሪፎርሙ ያግዛል ብለዋል፡፡
የዜጎች እንግልትና ኢ-ፍትሐዊ አገልግሎትን ለማስቀረት፣ በየደረጃዉ ያለ ሌብነትና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመቅረፍ ሪፎርም ትልቅ ሚና እንዳለዉ የቢሮዉ የከተማ ፕላን ጥናት መረጃና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ኃይሌ ተናግረዋል።
በስልጠና መድረክ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች አጥጋቢ ምላሽ ተሰጥቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.