በዘመናዊ ፕላን የምትመራ የለማችና የበለፀገች ከ...

image description
- ውስጥ ዜና    0

በዘመናዊ ፕላን የምትመራ የለማችና የበለፀገች ከተማ ሆና የማየት ራዕይን የሚያጠናክር የልማት ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡- አቶ አንዋር አክመል

ፕላንና ልማት ቢሮ፤ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ከተማዋን በፕላን በመምራት እና ልማቷን በማፋጠን ነዋሪዎቿን ተጠቃሚ የማድረግ ተልዕኮን ያነገበ የቀጣይ አምስት ዓመታት የልማት ዕቅድ ላይ ከቢሮዉ አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ተወያይቷል፡፡

በቢሮዉ የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዋር አክመል የልማት ዕቅዱ በከተማችን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገበዉን ጥራት ያለው ዕድገትና ሁለተናዊ ልማት የሚያስቀጥል የልማት ዓላማዎችና ግቦች ያሉት መሆኑን  የአምስት ዓመት (ከ2019-2023 በጀት ዓመት) የልማት ዕቅድ ባቀረቡበት ወቅት  ገልፀዋል፡፡  

የመካከለኛው ዘመን የልማት ዕቅዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የተቋማት የአምስት ዓመት የመካከለኛ ዘመን የልማት ፕላን አዘገጃጀት ቢጋርን የተከተለ መሆኑንም አክለዋል፡፡


 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.