'‘ዲጂታል ለልህቀት'’ በሚል ስያሜ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ፣ በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን፣ በአፍሪካ ቀዳሚ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ዛሬ በይፋ መርቀናል።
ይህ ታላቅ ስኬት ለሀገራችን ከፍተኛ ኩራት ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂ የሚመራ እና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት ምን ሊያስገኝ እንደሚችል ማረጋገጫ ነው። የኢኮኖሚ ወሳኝ መሠረተ ልማት የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የዜጎችን ጊዜ ይቆጥባል፣ የሙስና ቀዳዳዎችን ይደፍናል፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተቋማትን ታማኝነትና ጥንካሬ ያጎለብታል።
ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ተራ ምኞት ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር ነው። ይህን ስኬት እንድናጠናክር፣ ተሞክሯችንን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንድናካፍል፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንድንጓዝ ጥሪዬን አቀርባለሁ!
Today, at the 'Digital for Excellence' summit, we officially inaugurated the Unified MESOB Application, Africa's first unified digital service application that brings services from across institutions onto a single platform. This milestone is a source of immense national pride and a testament to what deliberate, focused investment in technology can deliver.
MESOB one-stop service is critical economic infrastructure. It saves citizens' time, closes corruption gaps, and strengthens institutional integrity on the government side. Above all, it stands as a clear demonstration that Ethiopia's ambitions are not wishes, they are realities we build with our own hands and our own capacity.
I call on us to consolidate this achievement, share this experience with our African brothers and sisters, and move forward with the determination to deliver even more!
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.