ዛሬ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጽዳት ንቅናቄ አስጀምረናል ።
የአንድ ከተማ ዓለም አቀፍ መለኪያው ፅዳት፣ ውበት እና ኢረንጓዴነት ነው። ለዚህም ነው ውብ፣ ፅዱ እና አረንጓዴ ከተማን ለመፍጠር ህዝባችንን አሳትፈን ባለድርሻ አካላትን በማነቃነቅ ውጤታማ ስራ ሰርተን አዲስ አበባን በአፍሪካ ከ10 ፅዱ ከተሞች እንዷ ለማድረግ የቻልነው።
አዲስ አበባ ከዚህ በፊት የምትወቀስበት ፅዱ እና ውብ አለመሆኗን እና የአረንጓዴ ከተማን ሽፋንዋ እየቀነሰ መሄዱን በሰራናቸው ተከታታይ ስራዎች መቀልበስ ችለናል።
ፅዳት የዘወትር ስራ ነው፤ ፅዳት ባህል መሆን መቻል አለበት። ሁልጊዜ ከህይወታችን እየንዳንዱ እንቅስቃሴ ጋር የተሳሰረ መሆኑን በሁሉም አካባቢ ማረጋገጥ ይኖርብናል።
ጽዳት ከቤት ይጀምራል። በመሆኑም ሁላችንም በየአካባቢያችን፤ በየተቋማችን ባህል አድርገን መያዝ ይገባናል። ይህንን ባህል እስኪሆን ያለእረፍት በትጋት በመስራት፣ ሁሌም ክትትል በማድረግ የፅዳት አምባሳደር እንድንሆን አደራ ማለት እፈልጋለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.