ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።
ዛሬ የከተማ አስተዳደራችንን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል።
ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በበጀት ዓመቱ ለመፈፀም ያስቀመጥናቸውን ግቦች፣ እንዲሁም የ2018 በጀት ዓመት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅዳችን ማጠቃለያ ዓመትም በመሆኑ ከባለፉት 5 ዓመታት አፈፃፀም ጋር አያይዘን የምንገመግም ይሆናል።
እንደሚታወቀው ባለፉት 5 ዓመታት ያቀድናቸውን ስትራቴጂክ ግቦች በተሟላ ሁኔታ ለመተግበር በታማኝነት፣ በቅንነት፥ ያለ እረፍት 24/7 ሰርተን በርካታ ውጤቶችን አስመዝግበናል።
በተለይም አዲስ አበባን ከማይጠቅሙ አጀንዳዎች አውጥተን የልማት እና የሰላም ማዕከል እንድትሆን አድርገናታል። እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ፅዱ፥ አረንጓዴ፣ ውብ እየሆነች በመምጣቷ የዓለም ትኩረትን ስባለች።
በእርግጥ ከስኬቶቻችን ባሻገር ዛሬም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች አሉብን። በተለይ የአመራራችን የውጤታማነት ልዩነቶች፣ በከተማችን የሚታዩ የኑሮ ውድነት እና ፍልሰት ችግሮችን በጥልቀት የምንገመግም ይሆናል።
በርካታ ስኬቶችን ብናስመዘግብም ከህዝቡ የመልማት ፍላጎት እና ከብልፅግና ግባችን አንፃር ብዙ ስለሚቀረን ስኬቶቻችንን ማስፋት፤ ተግዳሮቶች ደግሞ ለይተን መፍታት በቀጣይ በጀት ዓመት የላቀ ስኬት ማስመዝገብ የግምገማችን ማዕከል ይሆናል። በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችም ላይ እንወያያለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.