ስለ እኛ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ አጭር ታሪክ

  • image description

    አመሰራረት

    የአዲስ አበባ ከተማን በፕላን ለመምራት በማሰብ ከተማዋ ከተቆረቆረችበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ 10 የከተማ ልማት ፕላኖች(ማስተር ፕላኖች) ተዘጋጅቶለት ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ጥናቶችን ስታደርግ ቆይታለች፡፡ አሁንም በማድረግ ላይ ትገኛለት፡፡

    ከእነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ከተዘጋጁ የልማት ዕቅዶች/ፕላኖች መካከል በአሁኑ ወቅት ከተማዋን በዓለም አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ተወዳዳሪና ተመራጭ ከተሞች አንዷ ለማድረግ ታስቦ የ10ኛው የከተማው መሪ ፕላን(የ10 እና 25 ዓመት የዕድገት መሪ ፕላን) ተዘጋጅቶ በከተማው ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 52/2009 ፀድቆ ሥራ ላይ ይገኛል፡፡

  • image description

    የቢሮ ስልጣንና ኃላፊነት

    በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ አበባ ከተማ የአገሪቱና የአፍሪካ መዲና እንዲሁም የአለም አቀፍ ዲፕሎማሲና የአገሪቱ ትራንስፎርሜሽን ማፅከል በመሆን የምትጫወተውን ሚና በዓለም አቀፍ ደረጃ በላቀ ሁኔታ ተወዳዳሪና መስባዊ መሆን የሚያስችላትን ግብ ለማሣካት እንዲቻል የአ/አ ከተማ ፕላንና ልማት ኮሚሽን በከተማው ምክር ቤት ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 48/2009 እንደገናም የከተማዋን አስፈፃሚ አካል እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 64/2011 የተቋቋመ ህጋዊ ሰውነት ያለው የከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ የመንግስት መስሪያ ቤት ሆኖ እንዲቋቋምና ተጠሪነቱም ለከተማው ከንቲባ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

    በመቀጠልም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ለማቋቋም በወጣ አዋጅ ቁጥር 74/2014 ተጨማሪ ኃላፊነቶች ተሰጥተውት የተወሰነ ማሻሻያ በማድረግ እንዲዋቀር ተደርጓል።

    የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በቀረበው የአስፈፃሚ ተቋማት መልሶ ማቋቋም መሠረት ተቋሙ ከ#ኮሚሽን ፥ ወደ #_ቢሮ የተቋም ደረጃ በማደግ በአዲስ እንዲደራጅ ተደርጓል። በምክር ቤቱ የፀደቀው ስያሜውም "የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት #_ቢሮ" ነው።

    በመሆኑም ቢሮው በተሰጠው ስልጣን መሠረት በከተማው የሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በተበጣጠሰ ሁኔታ ይተገበር የነበረውን የስፓሻል ፕላንና የማህበራዊ ኢኮኖሚ የረጅምና የመካከለኛ ጊዜ የልማት ዕቅዶችን በማቀናጀት ውስን የሆነውን ሀብት ውጤታማ በሆነ አግባብ ለመፈፀም እንዲቻል በሴክተሮቸ ደረጃ የማህበራዊና ኢኮኖሚ ልማት ዕቅዶች ከስፓሻል ፕላን ተቀናጅተው መታቀዳቸውን፣ አፈዓፀምን የመከታተል፣ የመቆጣጠር፣ ክፍተቶችን ለይቶ አቅጣጫ የማስቀመጥ፣ የከተማውን ተጨባጭ ችግሮች ለመፍታት የሚያግዝ የከተማ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን የማከናወንና የከተማው መሪ ዕቅዶችና የአፈፃፀም ግምገማ ሪፖርቶችን የማዘጋጀት ዋና ዋና ተልዕኮዋችን በመወጣት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

    ይህ ተቋም በአሁኑ ጊዜ ቢሮውን በበላይነት የሚመሩት አንድ ዋና የቢሮ አላፊ አምስት ምክትል ቢሮ አላፊ ያሉት ሲሆን የዕለት ከዕለት ሥራውን ለማስፈፀም በ200 የሠው ኃይል በማዕከል ደረጃ ተደራጅቶ ይገኛል፡፡

የጎብኚዎች አስተያየት

ምንም አልተገኘም.

የቢሮው መዋቅር

ተልዕኮ

Conducting research and development by involving the society and stakeholders, preparing development plans and monitoring their performance, controlling, evaluating and measuring them, managing planning information with modern technology, leading the city with a plan and speeding up its development to benefit its residents.

ራዕይ

 "In 2022, Addis Ababa will be a thriving and prosperous city led by a modern plan!"

እሴቶች

 Servantship: To serve the institutions and the residents of the city faithfully and efficiently in terms of the tasks and responsibilities assigned to the Planning and Development Bureau by decree;
 Rule of law: To make the plan approved by law to be executed only legally;
 Liability: To indicate that carrying out the duties of the office outside of the established rules and regulations will result in liability;
 Participatory: Believing that it is important to create a sense of ownership by involving the relevant parties in the preparation and implementation of the development plan;
 Professionalism: It means that the management and the employee always strive to improve themselves in order to carry out the mission of the office with knowledge and skills.