ዳይሬክቶሬቶች

የከተማ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

አቶ

image description

የተቋሙን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አመታዊ ዕቅድ፤ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲጸድቅ ለፈፃሚዎች ያስተዋውቃል፣ በሥራ ላይ እዲውል ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ለዳይሬክቶሬቱ ሥራ የሚያገለግሉ የሰው ኃይል እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋላቸውንም ያረጋግጣል፣ የዳይሬክቶሬቱን ሥራ ለማከናወን ምቹ የሥራ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፣ የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በበላይነት ያስተባብራል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አስፈለጊውን ውሳኔ ይሰጣል፣ የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ አፈፃፀም ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ለቅርብ ኃላፊው በየጊዜው ስለሥራው ሪፖርት ያቀርባል፣ የጥናትና ምርምር ስራ የሚመራበት የዉስጥ አሠራር መመሪያ ያዘጋጃል፤ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደረጋል፣ አዳዲስ አዋጆች፣ ደንቦችና የአፈፃፀም መመርያዎችን ለዳይሬክቶሬቱ አባላት ያሳውቃል፣ አፈፃፀሙን ይከታተላል::