የሚጠየቁ ጥያቄዎች
የፕላን ጥሰት እና ሌሎች ጥቆማዎችን ያድርሱን
መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ፣ እባክዎን የእውቂያ ቅጹን ይጠቀሙ ወይም በኢሜል ወደ info@example.com ይላኩልን. aapdco@gmail.com
ኢኳቶሪያል ጊኒ መንገድ፣ 22 አለፍ እንዳሉ ለም ሆቴል አካባቢ፣ Addis Ababa, Ethiopia
- የከተማ አስተዳደሩን የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ ግብረ መልስ ይሰጣል፤ ይገመግማል፤ ይመዝናል፣ ደረጃ ያወጣል፣ ሪፖርት ለሚመለከተው ያቀርባል
- የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፣
- የአካባቢ ልማት ፕላን ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ሲፀድቅ ተግባራዊ መሆኑን ያረጋግጣል፣
- የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ፕላን ያዘጋጃል፤ ያፀድቃል፤ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፣
- የፕላን ዝግጅትና አተገባበር የጥናትና ምርምር ሥራዎች ያከናውናል፣ መረጃዎችን ይሰበስባል፣ ያቀነባብራል፤ ያሰራጫል፣
- በከተማ ፕላን ዝግጅት ወቅት የሕዝብ ተግባቦትና ስርፀት ሥራዎችን ያከናውናል፤ ተደራሽ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የመረጃ ስነዳና ስርጭት ቋት ያደራጃል፣ ጥቅም ላይ ያውላል፣
- የከተማው አስተዳደር ፕላን ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላት ድጋፍና ምክር ይሰጣል፣
- በሚያመነጫቸው ፖሊሲዎች፣ ሕጎች፣ ከተማ ፕላኖች፣ የልማት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች አካል ጉዳተኞች፣ አረጋዊያን፣ የሴቶችንና የወጣቶች ጉዳዮች እንዲካተቱ መደረጋቸውን ያረጋግጣል፣
- የከተማ ፕላን በሚጥስ ማናቸውም አካል ላይ በሕግ መሠረት እርምጃ ይወስዳል፤ ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፣
- ከተማ ፕላን ለማዘጋጀት የሚያስችል መሠረታዊ የከተማ ካርታ ከሳተላይት ምስሎች ከሀገሪቱ ጂኦዴቲክ ካርታ ጋር በተገናዘበ መልኩ ያዘጋጃል፤ እንዲዘጋጅ ያደርጋል፤ ያደራጃል፤ ያሰራጫል፣
- የፀደቀ ፕላን በሕግ መሠረት እንደየአግባቡ ያሻሽላል፤ ያጣጥማል፣
- የፕላን፣ የዲዛይንና የግንባታ ፈቃድ ደረጃዎችን አፈፃፀም የሚመለከቱ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ፕላን ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላት እንዲያቀርቡና የመስክ ምልከታ እና ጥናት በማድረግ ሪፖርት ያቀርባል፣
- የከተማውን ዝርዝር የሥነ-ህዝብ ጥናትና ትንበያ ያካሄዳል፣ ውጤቱንም ለከተማው አስተዳደር አካላትና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፤ የስነህዝብ ፖሊሲ በከተማው ውስጥ ይፈፅማል፤ ያስፈፅማል፣
- የከተማውን ዓመታዊ አጠቃላይ የምርት ዕድገት ለማስገኘት የሚያስፈልገውን የካፒታልና የምርታማነት ዕድገት መነሻዎችን ይገምታል፤ ውጤቱንም ለሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላትና ለባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፣
- የከተማውን የምርት ዕድገት ግቦች የፖሊሲና የህግ ሪፎርም እርምጃዎች ጋር የተጣጣሙ የቁጠባ፣ የኢንቨስትመንትና የወጪና የገቢ ንግድ ከተማ አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ግቦችን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፣
- ከአጠቃላይ ከተማ አቀፍ ምርት የኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት ዘርፎችና የከተማ ግብርና የተናጠል ድርሻን ይለያል፤ ውጤቱንም ለሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላትና ለባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፣
- የከተማውን በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች መካከል የሚኖረውን የግብዓት አቅርቦት ፍላጎት ይተነትናል፤ ውጤቱንም ለሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላትና ለባለድርሻ አካላት ያሰራጫል፣
- ከሚመለከታቸው የከተማው አስተዳደር አካላት ጋር ተከታታይ ምክክር በማድረግ የሚተገበሩ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን እንዲሁም ሊወሰዱ የሚገባቸውን የፖሊሲና የህግ ሪፎርም እርምጃዎችን የሚዘረዝር የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ የዘርፍ ፕላን ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፣
- ተዋረዳዊ አደረጃጀት ያላቸው የከተማው አስተዳደር አጠቃላይ ፕላን ተመጋጋቢ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ በየበኩላቸው የሚፈፅሟቸውን ተግባራት የሚያሳይ የተቀናጀ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ ልማት ፕላን አፈፃፀም መርሃ-ግብር ያዘጋጃል፤ ሲፀድቅም ተግባራዊ መሆኑን ይከታተላል፣
- በጸደቀው ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት በአስፈጻሚ ተቋማት የሚከናወኑ ነባርና አዲስ የካፒታል ፕሮጀክቶች ዕቅድን አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ለሚመለከተው አካ ሪፖርት ያቀርባል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማን በፕላን ለመምራት በማሰብ ከተማዋ ከተቆረቆረችበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ 10 የከተማ ልማት ፕላኖች(ማስተር ፕላኖች) ተዘጋጅቶለት ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ ጥናቶችን ስታደርግ ቆይታለች፡፡ አሁንም በማድረግ ላይ ትገኛለት፡፡
ከእነዚህ በተለያዩ ጊዜያት ከተዘጋጁ የልማት ዕቅዶች/ፕላኖች መካከል በአሁኑ ወቅት ከተማዋን በዓለም አቀፍ እና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ተወዳዳሪና ተመራጭ ከተሞች አንዷ ለማድረግ ታስቦ የ10ኛው የከተማው መሪ ፕላን(የ10 እና 25 ዓመት የዕድገት መሪ ፕላን) ተዘጋጅቶ በከተማው ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 52/2009 ፀድቆ ሥራ ላይ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ስር 4 ዘርፎች ይገኙበታል
ጥያቄህን ጠይቅ
መልሱን ከታች ማግኘት ካልቻሉ እባክዎን መልእክት ይላኩልን.