እንጦጦ ፕሮጀክት

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

እንጦጦ ፕሮጀክት

በዛሬው እለት እንጦጦ አካባቢ ለሚገኙ የደሃ ደሃ ለሆኑ እና ጫካ ውስጥ በማይመቹ ቦታዎች ሲኖሩ ለነበሩ የተለዩ እናቶች የከተማ አስተዳደሩ ካስገነባቸው የጉለሌ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ 44 ቤቶችን በመግዛት ድጋፍ ካደረጉልን ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፦

1. ቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን - በ16.8 ሚሊዮን ብር አሰር ስቱዲዮ

2. ቶኩማ ስታር ቢዝነስ - በ8.5 ሚሊዮን ብር ሁለት ስቱዲዮ እና ሁለት ባለ አንድ መኝታ

3. መሃመድ ሱጃጃ - በ10 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ

4. ጌታመሳይ ዘመድኩን - በ8.5 ሚሊዮን አምስት ስቱዲዮ

5. ኤም ደብልዩ አስ ትሬዲንግ - በ8.5 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ

6. ቲ ኤፍ ጂ ጀኔራል ትሬዲንግ- በ8.5 ሚሊዮን ብር አምስት ስቱዲዮ

7. ኖህ ሪልስቴት- በ5.3 ሚሊዮን ብር ሁለት ባለአንድ መኝታ ቤቶች

8. ዲሪባ ደፈርሻ - በ4.2 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ እና አንድ ባለ አንድ መኝታ

9. ማህደር ገብረመድህን ኃ/የተ/የግ/ ኩባኒያ - 4.2 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ እና አንድ ባለ አንድ መኝታ

10. አኮርዲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ- በ1.6 ሚሊዮን ብር አንድ ስቱዲዮ

ከላይ የተጠቀሱት ተቋማት እና ግለሰቦች በጠቅላላው 74.6 ሚሊዮን ብር የግንባታ ወጪ በመሸፈን 44 የመኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካማ የአካባቢው ነዋሪዎች ስላበረከቱ እያመሰገንን፣ በቀጣይም ድጋፍ ለማድረግ የምትፈልጉ ልበ-ቀና ባለሃብቶች የበኩላችሁን አስተዋፅዖ እንድትወጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.