የ2016 ግማሽ በጀት ዓመት እውቅናና ሽልማት መ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የ2016 ግማሽ በጀት ዓመት እውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር ተካሄደ

የ2016 ግማሽ በጀት ዓመት እውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር ተካሄደ

ሚያዚያ 04/2016:- የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የ2016 የመጀመሪያ ግማሽ በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ ጨምሮ የክፍለ ከተማ አጠቃላይ እንዲሁም የወረዳ ኮር አመራሮችና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ የክፍለ ከተማው ፕላን ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን ጫላ በምዘና ሂደት የነበሩ ጥንካሬዎችና ድክመቶችን አስመልክቶ ሪፖርት አቅርበዋል።

በጥንካሬ ከዚህ በፊት ከነበሩ ምዘናዎች አንፃር የተሻለ መናበብና ቅንጅት እንዲሁም የተሻለ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት መሆኑ እንዲሁም በድክመት ከመረጃ አያያዝና የእቅድና ሪፖርት ተናባቢነት አኳያ በቀጣይ መስተካል እንዳለባቸው ተመላክቷል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ አበራ ለተሸላሚዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለው እንዳሉት እውቅና ተሸላሚዎችን የሚያስደስት ሌሎችን ደግሞ የሚያነቃቃ እንዲሁም የፉክክርና የቁጭት ስሜት የሚፈጥር ብሎም ለቀጣይ ተግባር የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

ከእውቅና ባሻገር በፓርቲና መንግስት የተቀመጡ ግቦችን ማሳካትና የህዝባችንን ፍላጎት ሊያሟሉ የሚችሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታትና አገልግሎትን ማዘመን ከሁላችን የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም በክፍለ ከተማ ደረጃ ከተመዘኑ 33 ተቋማት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ እንዲሁም በወረዳ ደረጃ ከተመዘኑ 13 ተቋማት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

በዚህም መሰረት በክፍለ ከተማ ደረጃ

1ኛ የዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት

2ኛ ህብረተሰብ ተሳትፎ በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

3ኛ ግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ጽ/ቤት

በወረዳ ደረጃ

1ኛ ወረዳ ጀሞ

2ኛ ወረዳ 11

3ኛ ወረዳ 14 በመሆን እውቅናና ሽልማት አግኝተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.