እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረ...

image description
- ውስጥ ወቅታዊ ጉዳይ    0

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፡፡

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ፡፡

***

የኢድ-አል-ፈጥር ፆም ወቅት በእዝነት ፣ በመረዳዳትና በምህላ በመጠናቀቁ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1ሺህ 445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችው፡፡

በዓሉን ስናከብር እንደ ወትሮዉ ሁሉ የተቸገሩትን በመርዳት፣ ያለው ለሌለው በእዝነት በመደገፍና ማዕድ በማጋራት፣ ወገንን በመጠየቅ በአብሮነት ስሜት ተጋግዝነው ማክበር መልካም እሴታችን ነው፡፡

የረመዳን ወር መላው ሙስሊም ማኅበረሰብ በናፍቆትና በጉጉት የሚጠብቀው ወር ነው። ወሩ የአሕዛብ በሮች የሚዘጉበት፣ የጄነት በሮች ወለል ብለው የሚከፈቱበት ነው። ሙስሊሙ በጾምና በኢባዳ ከፈጣሪው ጋር የሚቀራረብበት፣ ዚክር የሚበዛበት ወር ነው፡፡

በዓሉን በሰላም፣ በመተሳሰብ፣ በበጎነት፣ በመተጋገዝ፣ በፍቅርና በምህረት ዕሴቶቻችን ተመስርተን እያከበርን የከተማችንን ብሎም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን እንድናደርግ እያልሁ በድጋሚ እንኳን ለ1ሺህ 445ኛው ለታላቁ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም፣ በፍቅር፣ በጤናና በሠላም አደረሳችሁ !! አደረሰን !!

ኢድ ሙባረክ !

ሚያዝያ 1፣ 2016 ዓ.ም

ዳዲ ወዳጆ (ዶ/ር)

የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.