- ውስጥ
ወቅታዊ ጉዳይ
0
ቢሮው ከማዕከል እስከ ከፍለ ከተማ ባካሄደዉ ክትትልና ድጋፍ ላይ ውይይት አደረገ፡፡
(ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ በ3ኛው ሩብ ዓመት ከማዕከል እስከ ከፍለ ከተማ በተደረገው ክትትልና ድጋፍ ላይ የማዕከል አመራሮች እና ሠራተኞች እንዲሁም የክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች ኃላፊዎች፣ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች በተገኙበት ውይይት አካሄደ፡፡
የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ዳዲ ወዳጆ(ዶ/ር) እንደተናገሩት ክትትልና ድጋፍ የተደረገው በዋናነት ለመደጋገፍና እንደ ተቋም የተሠጠን ተልዕኮ በጋራ ለመወጣት ነው በማለት ገልፀዋል፡፡
በቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ ሁሉአገረሽ ተፈራ የማዕከል የክትትልና ድጋፍ ሪፖርት ባቀረቡበት ጊዜ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡
በቢሮው የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ንጉሴ የክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽህፈት ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ክትትልና ድጋፉ በዋናነት ትኩረት ያደረገው፡- የሪፎርም ስራዎች፣ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ የቅንጅታዊ ስራዎች፣ የወረዳው መዋቅር ያለበት ሁኔታ፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራዎች፣ የኮሚኒኬሽና የሚዲያ ግንኙነት ስራዎች እና የፕላን ስራዎች አፈፃፀም ላይ መሆኑን አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም በቀረቡት ክትትልና ድጋፍ ሪፖርት ላይ በጥልቀት በመወያየትና በመገምገም በጥንካሬ የታዩ ጉዳዮችን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና በድክመት የታዩ ጉዳዮችን ደግሞ የሚመለከታቸው አካላት በቀጣይ ቀሪ ወራት ውስጥ ማስተካከል እንዳለባቸው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.