
የልደታ ክ/ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት በ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ጽ/ቤቶችና ወረዳዎች እውቅና ሰጠ።
በእውቅና ፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሰኢድ አሊ የላቀ ውጤት ያስመዘገበን አካል እውቅና መስጠት የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር በማድረግ የተሻለ የስራ ተነሳሽነትን የሚያላብስ በመሆኑ አጠናክረን መቀጠል አለብን ብለዋል።
አቶ ሰኢድ አክለውም ፈጣን ፣ቀልጣፋና ፍትሃዊ የሆነ አገልግሎት ለህብረተሰባችን በመስጠት በሁሉም ዘርፍ የክ/ከተማችን ነዋሪዎች ህይወት ሊቀይር የሚችል ስራ መሰራቱን ገልፀው በቀጣይም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መስራት አለብን ብለዋል::
የልደታ ክ/ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ክብረት አሳምነው በበኩላቸው አንድ እቅድ አንድ ሪፖርት የሚለውን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራታቸውን ተናግረዋል::
አቶ ክብረት አክለውም በተደረገው የቁልፍ ውጤት አመላካች (kpi) ምዘና 39 የክፍለ ከተማ ሴክተሮች መመዘናቸውን ገልፅው ከተመዘኑት ጽ/ቤቶች በጣም ከፍተኛ 10፣ ከፍተኛ 27 እና መካከለኛ 2 ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.