
ከተማችንን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ተባብረን የማይገፋ የመሰለውን ተግዳሮት እየተሻገርን ከተማችንን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ በላቀ ትጋት ማገልገላችንን እንቀጥላለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ በኮሪደር ልማት ሥራ ላይ ከተሠማሩ ሠራተኞች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች እንዲሁም አመራሮች ጋር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተገኝተን አበረታትተናል ብለዋል፡፡
ለተሽከርካሪ፣ ለእግረኛ እንዲሁም ለነዋሪዎች ምቹና ውብ አዲስ አበባን ለመገንባት በፕላኑ መሠረት ዲዛይን ከማዘጋጀት እስከ ግንባታ ድረስ ያለውን ሥራ በኃላፊነት ስሜት እየመሩ ላሉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.