
ከተሞችን ለዘላቂ ልማት እና ለነዋሪዎች ተጠቃሚነት ምቹ እንዲሆኑ በተቀናጀ ፕላን መመራት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡
ግንቦት 17-2016 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፕላንና ልማት ፅ/ቤት "የከተማ ፕላን ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ቃል በመዋቅራዊ ፕላንና ፕላን ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ከክ/ከተማ እና ከወረዳ ለተዉጣጡ የምክር ቤት አባላት፣ የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል፡፡
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ በቀለ ጉታ ከተማችን አዲስ አበባ የአፍሪካና የኢትዮጵያ መዲና ስለሆነች አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን የልማት ስራዎች ፕላኑን ታሳቢ አድርገዉ መፈፀም እንዳለባቸውና ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ለፕላን ልዩ ትኩረት በመስጠት የፕላን ጥሰትን በጋራ ልንከላከል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል::
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ በለጠ አለምነህ በበኩላቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ፕላኑ የከተማችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ልማቶችን በዘላቂነት የምናረጋግጥበት መሳሪያ በመሆኑ በእኔነት ስሜት በመያዝ አፈፃፀሙ ላይ የድርሻዉን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ በለጠ ጨምረውም መዲናችን አዲስ አበባ በ2022 ዓ.ም የምትደርስበትን ራዕይ ለማሳካት የልማት ስራዎች በመዋቅራዊ ፕላን መመሪዎችና ስታንዳርዶች መሠረት ተፈፃሚ ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ከተሞችን ለዘላቂ ልማት እና ለነዋሪዎች ተጠቃሚነት ምቹ እንዲሆኑ በተቀናጀ ፕላን መመራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም ከባለድርሻ አካላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በተጨማሪም በማህበራዊ ኢኮኖሚ ልማት እቅድ ዝግጅት ፣አፈፃፀም ፣ግምገማና ምዘና መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተሰርቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.