
ቢሮዉ የዓለም የነጭ ሪቫን ፣ የህጻናት እና የጸረ-ኤች አይ ቪ ኤድስ ቀንን አከበረ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች የአለም የነጭ ሪቫን "የሴቷ ጥቃት የኔም ነዉ ዝም አልልም" ፣የህፃናት "ህፃናት የሚሉት አላቸዉ እናዳምጣቸዉ" እና የፀረ- ኤች አይ ቪ ኤድስ "ሰብዓዊ መብትን ያከበረ የፀረ-ኤች አይ ቪ አገልግሎት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል አከበሩ።
የዓለም የነጭ ሪቫንና የህጻናት ቀን በዓለም አቀፍ ለ33ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ እንዲሁም የፀረ- ኤች አይ ቪ ኤድስ ደግሞ በዓለም አቀፍ ለ37ኛ በሀገራችን ለ36ኛ ጊዜ እንደሚከበር ተገልጿል ።
በቢሮው የፕላንና ልማት ቢሮ የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ተረፈ በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለጹት ለነገ የተሻለች ሀገር ለመገንባት ዛሬ ህጻናትን ልናዳምጣቸዉ፣ መብታቸዉን ልናከብርና ጥሩ ስብዕና ተላብሰዉ እንዲያድጉ አዕምሯቸዉ ላይ ልንሰራ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ የሕፃናት ከፍተኛ ባለሙያ ወይዘሮ ራሄል ሙሉጌታ የበዓሉን ቀን አስመልክቶ ስልጠና በሰጡበት ጊዜ እንደተናገሩት ህጻናት ሀሳባቸዉን በነጻነት እንዲገልጹ ማበረታታትና ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የሴትን ጥቃት ሁሉም ማህበረሰብ በመቃወም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበትም ወይዘሮ ራሄል አክለውም ተናግረዋል።
በቢሮዉ የመረጃና ስታስቲክስ ባለሙያ አቶ ምላሹ ሀድጎ በፀረ-ኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ አቅርበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.