
ቢሮው በመንግስት ሰራተኞች አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ እና ከደሞዝ ስኬል ጣሪያ በላይ የአከፋፈል ስርዓት ላይ ኦረንቴሽን ሰጠ
የአዲስ አበባ ከተማ አስታዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብ ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ስራ አመራር ዘርፍ ከማዕከል ተቋማት እና ከክ/ከተማ ለተውጣጡ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች በመንግስት ሰራተኞች አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ስኬል እና በደሞዝ ማሻሻያ ሰንጠረዥ ከደሞዝ ስኬል ጣሪያ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የደሞዝ አከፋፈል ስርዓት ላይ ገለፃ አድርጓል፡፡
በገለፃው በዋናነት በደሞዝ ማሻሻያ ሰንጠረዥ ከደሞዝ ስኬል ጣሪያ በላይ ለሚሆኑ ሰራተኞች የደሞዝ አከፋፈል ስርዓት፣ ከደረጃ መደብ አንፃር፣ ከኮንትራት ቀጥር አንፃር፣ በድልድል ዝቅ የተደረጉ የደሞዝ ማሻሻያ ሂደት እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ዝርዝር ገለፃ ተሰጥቷል።
ዘገባው :-የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.