
የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽሉና የከተማዋን ተቀዳሚ ፍላጎት የሚመልሱ የፕላን ጥናቶች በጥራት እንዲዘጋጁ እየሰራን ነው፡- አቶ አደም ኑሪ
መልዕክቱ የቢሮዉ ጠቅላላ ካውንስል ከተዋረድ ካዉንስል ጋር የህዳር ወር የስራ አፈፃፀምን በገመገመበት ወቅት የተላለፈ ነው፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ጠቅላላ ካውንስል ከተዋረድ ካዉንስል ጋር የህዳር ወር የስራ አፈፃፀምን፣ የብልሹ አሰራር ማክሰሚያዎችን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና መፍትሔዎቻቸው ላይ ተወያይቶ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የቢሮው ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ በቢሮ ተዘጋጅተው የሚተገበሩ የአካባቢ ልማት ፕላኖች፣ የመሰረተ-ልማትና የሠፈር ልማት ፕላን ዲዛይን ጥናቶች እንዲሁም የመዋቅራዊ ለውጥ መረጃዎች የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽሉና የከተማዋን ተቀዳሚ ፍላጎት የሚመልሱ ሆነው በጥራት መከናወን እንዳለባቸው በስራ ግምገማ ወቅት ገልፀዋል፡፡
በቢሮዉ የዕቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አንዋር አክመል የ2017 በጀት ዓመት የህዳር ወር የስራ አፈፃፀምን፣ የብልሹ አሰራር ማክሰሚያ ስልቶችን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡
አቶ አንዋር በሪፖርታቸው የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጅቶች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ወጥ አሰራር እየተከተለ መሆኑን፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የማይሰተናገዱበት ምክንያት መለየታቸውን፣ የመዋቅራዊ ለውጥ ማሻሻያ መረጃዎች በአግባቡ እየተደራጁ መሆኑን፣ በ10 እና 5 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ያላናበቡ ተቋማት ክትትል መደረጉን፣ ተደራሽ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የከተማውን የ’ዕቅድና ሪፖርት’ ሲስተም እስከ ወረዳ ለመተግበር ጅምሮች መኖራቸውን በጥንካሬ ገልፀዋል፡፡
ከተዋረዳዊ ካውንስል ተሳታፊዎች መካከል የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ኃይማኖት ደውሼ በበኩላቸው በማምረቻና ማከማቻ የመሬት አጠቃቀም ምድብ የአካባቢ ልማት ፕላን ለማዘጋጀት መረጃ እየሰበሰቡ መሆኑንና ከክፍለ ከተማ ፕላን ተግባሪ ተቋማት ጋር በፈጠሩት የቅንጅታዊ አሰራር ስምምነት ቀልጣፋ አገልግሎት እና የመረጃ ልውውጥ እንዳለ ገልፀዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.