
የመዋቅራዊ ፕላን ማሻሻያ ጥናት አዳዲስ የፕላን እሳቤዎችን ያካተተ ነው፡፡
ፕላንና ልማት ቢሮ (የካቲት 9 ቀን 2017 ዓ.ም)፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት እና ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በሁለተኛው ዙር የመዋቅራዊ ፕላን ማሻሻያ ጥናት ላይ የማጠቃለያ ግብዓቶችን ሰበሰበ፡፡
የቢሮዉ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ ቢሮዉ መዋቅራዊ ፕላኑን የሚያሻሽለው በአጥጋቢ ምክንያቶችና በጥናት ላይ ተመስርቶ ብቻ ሳይሆን ከፀደቀው ፕላን ጋር በማገናዘብ መርምሮና ገምግሞ ነው ብለዋል፡፡ ለፕላን ቦርድ እንደሚያቀርብም በአዋጅ ቁጥር 52/2009 ተደንግጓል፡፡ አዋጁ ላይ በመመስረትም በሁለተኛው ዙር የመዋቅራዊ ማሻሻያ ጥናት ላይ ከሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላትና ፕላን ተግባሪ ተቋማት ጋር በመወያየት የማጠቃለያ ግብዓቶች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን አቶ አደም ገልፀዋል፡፡
በቢሮዉ የመዋቅራዊ ፕላን ማጣጣምና ምላሽ ሰጪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዑመር ደሴ በበኩላቸው ፕላኑን ለማሻሻል እንደምክንያት የቀረቡ ጉዳዮች ውስጥ ከከተማአቅፍ ፋይዳ ያላቸው የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎች፣ በኮሪደር የለሙና እየለሙ ካሉት መሰረተልማቶች (ተርሚናሎች፣ ፓርኮች፣ አረንጓዴ ቦታዎች፣ የወንዝ መጠበቂያ ስፍራዎች፣ የወንዝ ዳርቻዎች) ጋር የሚገኛይገኛሉ ብለዋል፡፡
አቶ ዑመር አክለውም ከህንፃ ከፍታ፣ ከመንገድና መጓጓዣ ጋር የተገናኙ አዳዲስ እሳቤዎችም በጥናት ማሻሻያነት ከቀረቡ ጉዳዮች ውስጥ እንደተካተቱ ገልፀዋል፡፡ በፕላን ትግበራ ወቅት በተቋሙ እንደችግር የተለዩ የመልካም አስተደዳር ችግሮችን መፍታትም ሌላው የጥናቱ ምክንያት ሆኖ ተጠቅሷል፡፡
የቢሮዉ ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደገለፁት የሁለተኛው ዙር የመዋቅራዊ ማሻሻያ ጥናቶች ከመንገድና መጓጓዣ፣ ከህንፃ ከፍታ፣ ከአረንጓዴ መሰረተልማት፣ ከመሬት አጠቃቀም፣ ከወረዳ ማዕከላት አንፃር በቀረቡት መሰረት ግብዓቶች ተሰብስበዋል፡፡ የማሻሻያ ጥያቄዎቹ ተገቢነት ከፕላን ጋር ተገናዝቦ በሚመለከተው አካል ከፀደቁ በኃላ የፕላኑ አካል ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን Like, Follow, subscribe በማድረግ ያግኙ
***
tiktok: https://www.tiktok.com/@addis.plan.bureau
website: www.aapdb.gov.et
Telegram፡- https://t.me/AddissAbabaPlanDevelopmentBureau
Twitter- https://twitter.com/PlanDevt_Bureau
YouTube - https://www.youtube.com/@addisababaplancommission1125
Facebook፡- https://www.facebook.com/addisababaplananddevelopment
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.