ቢሮው በተለያዩ ረቂቅ ጥናቶች ላይ ውይይትና ምክ...

image description
- ውስጥ ወቅታዊ ጉዳይ    0

ቢሮው በተለያዩ ረቂቅ ጥናቶች ላይ ውይይትና ምክክር አደረገ፡፡

 

(ፕላንና ልማት ቢሮ፣ ህዳር 01/2018 ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላን ልማት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንሲል የ11ኛው አዲስ አበባ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት ፕሮጄክት ጽ/ቤት ማቋቋሚያ ደንብ፣ አደረጃጃት እና የበጀት ዕቅድ ረቂቅ ጥናቶች ቀርበው ውይይትና ምክክር አድርገዋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ  አቶ አደም ኑሪ እንደገለጹት የጥናቱ ዓላማው ከተማዋን ለቀጣይ አስር ዓመት የሚያገለግል መዋቅራዊ ፕላን በማዘጋጀት ከወቅታዊ፣ አለምአቀፋዊና ሀገራዊ ከሆኑ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ጋር ለማጣጣም ነው ብለዋል፡፡

አቶ አደም ኑሪ አያይዘውም የተጀመረውን የከተማዋን ስማርት ሲቲ ግንባታ ቀጣይነት የሚያረጋገጥ 11ኛውን መዋቅራዊ ፕላን ለማዘጋጀት የተሻለ የከተማ ፕላን ስልቶች፣ ፅንሰ- ሀሳቦች እና መርሆዎችን መከተል አስፈላጊ መሆኑን አክለውም ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ረቂቅ ጥናቶች ላይ ጥናቶቹን ን የሚያዳብሩ ገንቢ ሀሳቦችና አስተያየቶች ተሰጥቶት በቀጣይ ተሻሽሎ እንዲቀርቡ አቅጣጫዎች ተሰጥቷል


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.