የስፓሻል ኘላን አፈፃፀም ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት
ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ወ/ሮ መዓዛ መንገስቱ

የተቋሙን ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን አመታዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፣ ሲጸድቅ ለፈፃሚዎች ያስተዋውቃል፣ በሥራ ላይ እዲውል ያደርጋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ለዳይሬክቶሬቱ ሥራ የሚያገለግሉ የሰው ኃይል እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋላቸውንም ያረጋግጣል፣ የዳይሬክቶሬቱን ሥራ ለማከናወን ምቹ የሥራ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፣ የዳይሬክቶሬቱን ሥራ በበላይነት ያስተባብራል፣ ያደራጃል፣ ይመራል፣ ይቆጣጠራል፣ ውሳኔ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አስፈለጊውን ውሳኔ ይሰጣል፣ የዳይሬክቶሬቱን ዕቅድ አፈፃፀም ይገመግማል፣ ግብረ-መልስ ይሰጣል፣ ለቅርብ ኃላፊው በየጊዜው ስለሥራው ሪፖርት ያቀርባል፣ ከፕላን ተግባሪ ተቋማት የሚቀርቡ የመብት ፈጠራ፣ ይዞታ ምዝገባ እና የግንባታ ፈቃድ አገልግሎት የተሰጠባቸው መረጃዎች እየገመገመ በስራ ድርሻቸው መሰረት ለቡድኖች ይመራል፣ ከቡድኑ አስተያየት ተሰጥቶባቸው የቀረቡ መረጃዎችን ከፕላን መረጃዎች ጋር በማመሳከር ይገመግማል፣ የቀረበው መረጃ የመስክ ምልከታ የሚያስፈልገው ከሆነ የመስክ መረጃዎችን በመውሰድ ከፕላኑ ጋር ያገናዝባል፣ ከቡድን መሪው የተሰጠው አስተያየት ስህተት ያለበት ወይም ያልተሟላ ከሆነ በድጋሚ እንዲታይ ከአስተያየት ጋር ይመልሳል፤ ከፕላኑ አንጻር ችግር የሌለባቸውን የመብት ፈጠራ እና የግንባታ ፈቃድ መረጃዎችን በቤዝማፕ እንዲወራረሱ ያስተባብራል መረጃውንም ለዘርፉ ያስተላልፋል፤ ከቡድኑ የተሰጠው አስተያየት ትክክለኛ መሆኑን ሲያረጋግጥ የፕላን ጥሰት የተፈጸመባቸውን መረጃዎች በመለየት ለዘርፉ ያሳውቃል፤ ከክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት እንዲወራረሱ ለማእከል የተላኩ የመብት ፈጠራ፣ ይዞታ ምዝገባ እና ግንባታ ፈቃድ አገልግሎት የተሰጠባቸው መረጃዎች እንዲገመገሙ ያስተባብራል፣ ከመዋቅራዊ ፕላን፣ አካባቢ ልማት ፕላን፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ከፕላንና ከስታንደርድ ጋር ልዩነት ያለባቸውን መረጃዎች እንዲስተካከሉ ለዘርፉ ያሳውቃል፤ ለክፍለ ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተሰጠው አስተያየት ትክክለኛ መሆኑን ሲያረጋግጥ የፕላን ጥሰት የተፈጸመባቸውን መረጃዎች ላይ የፕላን አፈጻጸምም ኦዲት ስራ እንዲሰራ ለዘርፉ ያሳውቃል፤ ከተለያየ አቅጣጫ የሚመጡ የፕላን ጥሰት ጥቆማ መረጃዎችን ተቀብሎ እንዲጣሩ ለሚመለከተው ቡድን ይመራል፣ አፈፃፀሙን በቅርብ ይከታተላል፣ የአካባቢ ሁኔታ እና የመሰረተ ልማት ክትትልና ቁጥጥር አስመልክቶ የተዘጋጁ ሪፖርቶችን ይገመግማል፤ የአካባቢ ሁኔታ እና የመሰረተ ልማት ክትትልና ቁጥጥር ሪፖረቶች ላይ የተሰጠው አስተያየት ስህተት ያለበት ወይም ያልተሟላ ከሆነ በድጋሚ እንዲታይ ከአስተያየት ጋር ይመልሳል፤ በክትትልና ቁጥጥር ሪፖርት ላይ የተሰጠው አስተያየት ትክክለኛ መሆኑን ሲያረጋግጥ የፕላን ጥሰት የተፈጸመባቸውን መረጃዎች በመለየት ለዘርፉ ያሳውቃል ::